ጀበርቲ ኤርትራውያን ምስ ኣሕዋቶም ጀበርቲ ኢትዮጵያ ርኽክባቶም የደላድሉ

መበገሲ ሓሳብ

ምንጪ: https://www.facebook.com/permalink.php?story_fbid=717167858639042&id=100010375026633

ኢትዮጵያዊያኑን ጀበርቲዎችንና ኤርትራዊያኑን ጀበርቲዎች በአንድ መድረክ ያስተሳሰረዉ በአዳማ ከተማ ራስ ሆቴል የተካሄደዉ በአርጎባ ህዝብ የስያሜ ለዉጥ ላይ ያተኮረ ጥናታዊ ጽሑፍ እና የዉይይት መድረክ! – ይሄን ይመስል ነበር፡፡ ያንብቡት እዚያዉ የነበሩ ያህል ይሰማዎታል! 

ወንድም ሙኽታር ዑመር እና አባዬ ዉይይቱ እስኪጀመር በባህል ቡድኑ በመታገዝ መድረኩን የሆነ ሞቅታ ያለዉ ድባብ እየቸሩት ነዉ፡፡ ‹‹ኑሩ ሠላም ዓላ፣ ሐቢቢ ሠላም ዓላ›› በሚሉና ‹‹አላሁ ዳኢሙ፣ ዳኢሙ›› በሚሉ ነሺዳ ጠቀስ ጨዋታዎች፣ በነበረዉ ጣዕመ ዜማ የጥንቱን የአባቶቻችንን ያን የከፍታና የደስታ ዘመን እያስታወስን ጥቂትም ቢሆን የኋልዮሽ ተጓዝን!! ያ .. ዘመን ዉዱ ዘመን!! …

የመድረኩ ተሳታፊዎች በተለያዩ የሀገራችን ክፍል የሞኖሩ የአርጎባ ተወላጆች፣ ኤርትራዊያን ጀበርቲዎች፣ ሙሁራኖች፣ ባላሀብቶችና ወጣቶች የነበሩ ሲሆን ጥናታዊ ጽሑፉም የሚያጠነጥነዉ በአርጎባ ህዝብ ማንነት እና በማሕበረሰቡ መጠርያ ስያሜ ላይ ነዉ፡፡ ጥናታዊ ጽሑፉ ተዘጋጅቶ የቀረበዉ እንቁ በሆኑ እና ታላቅ ተስፋ በተጣለባቸዉ አቶ ሙሐመድ አቡበክር፣ በኑረላህ ከድርና እንዲሁም በዩሱፍ ሙሐመድ ከፍተኛ ድካምና ልፋት በኋላ የተዘጋጀ መሆኑና ጥናታዊ ጽሑፉም ከ3ዓመት በላይ እደፈጀ ከመድረኩ ተገልጧል፡፡ የዉይይት መድረኩን በዋናነት የመሩት በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ምድር ተመራማሪ የሆኑት ረዳት ፕሮፌሰር ተማም አወል በሽር ናቸዉ፡፡ 

ከወልቃይት ልዩ ቦታዋ ‹ኮረም› በመባል ከምትታወቀዉና ታላላቅ ዑለማኦችን ካፈለቀችዉ ምድር የተገኙት የራያዉ አርጎባ ታላቁ ዓሊም ሸይኽ አሕመደል ኩረማ (አሕመድ አል-ኮረም) ፕሮግራሙን በሚማርክ ዱዓ መከፈቱን ካበሰሩ በኋላ ወደ ዋናዉ ዱዳይ ተገብቷል፡፡

#በጥናታዊ_ዉስጥ_የቀረቡ_ሀሳቦች!!
የመጀመርያዉ ዘዉግ ስለ አርጎባ ማሕበረሰብ በጥቂቱ የሚያስዳስስ ክፍል ሲሆን፤ እሱም የአርጎባ ሕዝብ በቀደሙት ጊዜያት ነገደ እስላም፣ ጀበርት፣ የይፋት ህዝቦች፣ ወላስማዎች፣ የይፋትና የሀረርጌ ሙስሊም በሚል ይጠራና ይታወቅ እንደነበር የሚያረገነዝብ ነዉ፡፡ 

በሁለተኛ ደረጃ በጀበርት ስያሜና ታሪካዊ ዳራ ላይ የተደረገዉ የጥናቱ ዋና ክፍል ሲሆን ረዘም ያላ ቦዲ ያካተተ ክፍል ነዉ፡፡ ስለ ጀበርት መነሻና መድረሻ እንዲሁም ማነነትና ጠቅለል ያለ ይዘት በዕለቱ ከቀረቡ ጥናታዊ ጽሑፎች በመንተራስ ከማስታወሻ ማሕደሬ ካሰፈርኳቸዉና የጻፍኳቸዉ አንዳንድ ነጥቦች የቃላት እርምት በማድረግ በምሽቱ ክፍለ ጊዜ እንደማቀርብ ቃል እየገባሁ አሁን በእለቱ ወደ ወደ ተሰጡ ሀሳብና አስተያየቶች እንዲሁም ጥያቄዎች ላምራቹህ፡-

#ከመድረኩ_ተሳታፊዎች_የተነሱ_አስተያቶችና_ጥያቄዎች፡-
ሀሳብና አስተያየቶች እንዲሁም ጥያቄዎች የተሰነዘረዉ በጥዋቱ ክፍለ ጊዜ ሲሆን በከሰዓቱ ክፈለ ጊዜ ማብራሪያና መልስ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ የመጀመርያዉ አስተያየት ሰጪ አንደበተ-ርቱዑና እጅግ አዋቂ ብሎም ተናጋሪ የሆኑት ከላይ ቀደም ብለን ያወሳናቸዉ ዓሊም ሸህ አሕመደል ኩረማ (አሕመድ ኢብራሒም) የአርጎባ ህዝብ ታሪክና ማንነቱ ተቀብሮና አቧራ ለብሶ የኖረዉ እንዲሁም መታወቅ ያለበትን ያህል ያልታወቀዉ ታሪኩ በዓረብኛ ቋንቋ ተፅፎ በመቀመጡ መሆኑን ገልጸዉ መጽሐፍቶቹ ብዙሀን በሚረዳዉ በሚገባው ቋንቋ መከተብ እና መጻፍ እንዳለባቸዉ ወጣቶቹን አስገንዝበዋል፡፡ ለዚህም የአርጎባንና አርጎባዎች ታሪክ የያዙ በርካታ ኪታቦችን ማንበባቸዉን፥ ሆኖም ግን ያነበቧቸዉ መጽሐፍቶች በዐረብኛ የተደረሱ መሆናቸዉን አስምረዉ ብዞዎች ግን ሳያዉቋቸዉ ለመቅረቱም ይህ አንዱና ዐብይ ምክንያት አድርገዉ ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ ዉስጥ አሉ የተባሉ መላ ዑለማኦች አርጎባዎች እና ከአርጎባ ማንነት ጋር ተያያዥነት ያላቸዉ ናቸዉ፣ አኔም ጀበርቲነቴን እና አርጎብነቴን በጣም እወደዋለሁ፤ ሆኖም ግን እነዚያን የአርጎባ ዑለማኦችን የምረጠራቸዉ አርጎባ ብዬ ሳይሆን ‹ሸኾች› ብዬ ነዉ፣ እነርሱ የሁሉም ሀብትና ንብረት ናቸዉና በማለት ታላቅ ይዘት ያለዉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ ሲቀጥሉምስለሆነም ‹እራሳቸዉን የደበቁ ለዘለዐለሙ ይረሳሉ› በማለት አርጎባ ተቀበረ ማለት ኢትዮጵያ ተቀበረች ማለት ነዉ ሲሉም አክለዋለዉ ወጣቶች ዲናቸዉንና ታሪካቸዉን ጠብቀዉ እንዲሄዱ ዘክረዋል፡፡

በሁለተኛ ደረጃ ከመድረኩ ተሳታፊዎች የተሠነሱት ሀሳብና አስተያቶ ዉስጥ ጥናቱ ለእያንዳንዱ ተሳታፊ በሰነድ ለምን ሳይቀርብ ቀረ፣ ሰነዱ በእጃችን ቢደርሰን ኖሮ መስተካከል ያለባቸዉ እና ክፍተት ያላቸዉን አንዳንድ ጉዳዮች መመልከት እንችል ነበር፡፡ ጥናት አቅራቢዎቹ በጥናቱ ወቅት የገጠማቸዉን ቻሌንጆች እና ፈተናዎች ምንም እንኳን በመድረኩ ላይ የገለጹ ቢሆንም በሰነዱ ላይ ያለማካተታቸዉ ግን እንደ ክፍተት ተነስቷል፡፡ ይህንንም አስተያየት ተከትሎ የመድረኩ አዘጋጆች የጥናቱን ሰነድ በሀርድ ኮፒ እያንዳንዱ ተሳታፊ እጅ ለማድረስ ችለዋል፡፡ የመድረኩ አዘጋጆች ተሯሩጠዉ ላዘጋጁትና ላደረጉት ቅጽበታዊ ምላሽ እኔ እንደራሴ እራሴን ወክዬ ሳላመሰግናቸዉ አላልፍም፡፡ በተለይ ወንድም ኑርሑሴን ሙሐመድን እና ሌሎችንም ..

ከሰሜን ሸዋ ቀወት ወረዳ የመጡ ተሳታፊ ብዙ ቁም ነገር ላቸዉ ንግግሮችን ካደጉ በኋላ ታሪካችን በዓብኛ መጻፉ በአንድ ጎኖ ጠቅሟል፡፡ አጼዎቹ ቋንቋዉን ባለመረዳታቸዉ እንዳቃጠል፣ እስከመጨረሻዉ እንዳያጠፉብን ረድቷል፡፡ ለአብነትም ይይፋትና የአዳል ሱልጣኔትን ታሪክ የያዘዉ ፉትሑል ሀበሽ መጽሐፍ በቤቱ የተገኘበት ሰዉ ይገደል እንደነበር በማስታወስ፡፡ ይህንንም ተከትሎ በፕሮግራሙ መገባደጃ አካቢበ ሸህ አሕመደል ኩረማ የአንድ ታላቅ ዓሊምን ስም ጠቅሰዉ እና 500 ኪታብ ያህል የጻፉ ሰዉ መሆናቸዉን ገልጸዉ ከዚያ ሁሉ ግን ዛሬ ላይ የሚገኙት 25ቱ ብቻ ናቸዉ፤ ሌሎቹን መጽሐፍቶች አጼዎቹ እንዳያወድሙባቸዉ በመስጋት ከመሬት ስር ቀብረዋቸዉ አልፈዋል፡፡ እነሱን ፈልገን ፈልጎ የማግኘቱ ስራ የእኛ ድርሻ ነዉ ሲሉም አክለዋል፡፡ እንዲሁም ሸህ ሙሀመድ ዑመር (ከመኮይ) የተለያዩ ገንቢ የሆኑና በታሪክና በቅርስ ደረጃ ያሉ የየአካባቢያቸዉን ሁነቶች ገልጸዋል፡፡ ሆኖም ሀሳቦቻቸዉ ከርእሱ ጋር ብዙም ተያያዝ ባለመሆኑ በዝርዝር ለማቅረብ ይሰፋብናል ብለን ትተነዋል፡፡ ከዚህ በመቀጠል ለጥናቱ አቅራቢዎችና ለመድረኩ ጥያቄ ነክ ሀሳቦችን ያቀረበዉ ወጣት ጃዕፈር ሸህማሕሙድ ሲሆን ጥያቄዎቹም የሚከተሉት ናቸዉ፡፡

1. ጥናቱ በተለያዩ በዉጪ ሀገራት የሚኖሩ መላ ጀበርቲያኑን እንዴት ለማስተሳሰር እንደታሰበ ምንምድነዉ ያነሳዉ ሀሳብ
2. የጥናቱ ጥቅምና ፋይዳ ምንድን ነዉ
3. ስለማንነት ስናነሳ ከፖለቲካም ጋር ተያያዥ ነዉና አርጎባ ከመባላችን ይልቅ ጀበርቲ መባላችን ፖለቲካዊ ጥቅሙ ምንድነዉ
4. ከዚህ ጥናት ይልቅ ሪፎርም ማድረግ አይቀድምም ወይ ሪፎርሙስ ለጥናቱ ግብኣት ሆነዉ አልነበር ወይ
5. በአማራ፣ በአፋር፣ በሀረሪ እና በኦሮምያ ክልል ያለዉ አርጎባ አንድ አይነት ስነልቦና የለዉም፡፡ ይህንን ነገር ለምን መፍታት አልተቻለም፡፡ ጀበርቲ መባላችን ለዚህ መፍትሔ ሆነዋል ወይ የሚሉ በርካታ ጥያቄዎችን ያነሳ ሲሆን
ሌሎች ተሳታፊዎች ደግሞ በስያሜዉ ዙርያ፡- ጀበርቲ የአርጎባ ስያሜ ብቻ አይደለም ይልቁንም የወል ስም ተደርጎ ተወስዶ ተመልክተናል፡፡ ይህም መላዉ የሐበሻ ሙስሊሞች ጀበርቲ ተብለዉ ይጠሩም እንደነበር በታሪክ ተነግሯልና ጥናቱ ይህንን ነገር እንዴት ይመረምረዋል የአርጎባ ህዝብስ ስሙን ምን ያህል ያዉቀዋል ከብሔረሰብ ወደ ማህበረሰብ አይለዉጠንም ወይ የሚሉ ወሳኝ ይዘት ያላቸዉን ነጥቦች ለመድረኩ ወርዉረዋል፡፡ ከተሳታፊዎች የተነሱ ሌሎች ጥያቄዎች ይህ ጥናት በማሕበረሰቡ ዘንድ ዉዝዥንብር አይፈጥርም ወይ ይህን ሀሳብ ለምን አሁን ላይ ማንሳት አስፈለገ ከዚህ በፊት ሌላ መሰራት የነበረበት ነገር (ሪፎርሙ) መካሄድ አልነበረበት ነበር ወይ 
ሌሎች አካባቢ ከሚኖሩ የጀበርቲ ህዘቦች ጋር ያለን የቋንቋ፣ የባህል፣ እና የማንነት መመሳሰል (ልክ በኤርትራ፣ በጅቡቲ እና በኢትዮጵያ የሚኖሩ አፋሮች ያላቸዉን የቋንቋ እና የባህል መመሳሰል) አይነት እኛስ አለን ወይ ጀበርቲ ተብሎ ለመቀየር የተፈለገበት ምክንያት አርጎባ ተብለን ያጣነዉ ነገር ምንድ ነዉ እና ነዉ የሚሉ በርካታ ሀሳብና አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን በከሰዓቱ ፕሮግራም ከጥናት አቅራቢዎቹ እና ከመድረክ መሪዎቹ እንዲሁ ከተሳታፊዉም ጭምር እንደሚከተለዉ መልስ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

#ለተነሱ_ጥያቄዎች_የተሰጡ_መልሶች
ረዳት ፕሮፌሰር ተማም አወል በሽር የጥናቱ ጥቅምና ፋይዳ ምንድነዉ በሚለዉና አርጎባ ተብሎ ከመጠራት የታጣዉ ነገር እንዲሁም ጀበርቲ ተብሎ የሚገኘዉ ፖለቲካዊ ፋይዳ ምንድነዉ፣ በተለያዩ ክልሎችና ሀገራት ያለዉን የተለያየ ስነልቦና ያለዉን ህዝብ ምን የሚፈይደዉ ነገር አለ ለሚሉት በርካታ ተያያዝ ጥያቄዎች በሰጡት ማብራሪያ እንዳሉት፡- ጉዳዩ ጥቅም የማግኘት እና ያለማግኘት ብቻ ሳይሆን ጉዳዩ ትክክለኛ ማንነትን ፈልጎ የማግኘት ነዉ፡፡ ጥናቱ ዉጤት ቢገኝለትም ዉጤት ነዉ፤ ባይገኝለትም ዉጤት ነዉ፡፡ ጥናቱ ከመነሻ ነጥባችን ጋር ማች ካደረገ ትክክለኛና የኛ የሆነዉ የጥንት መጠርያ ስያሜያችን ጀበርት መሆኑ ነዉና በጀበርቲነታችን እንድንቀጥል ያደርገናል፤ ጀበርቲነታን ቀጠለ ማለት ደግሞ በዉጪም በሀገር ዉስጥም ካለ ሰፊሁ ከመላዉ የጀበርቲ ህዝብ ጋር ያለን የዝምድና ትስስር ተጠናክሮ ቤተሰባዊ መዋቅራችን ዳግም እንዲያድግ ደርገዋል፡፡ ለዚህም ማሳያ ዛሬ ከኤርትራ ምድር የተገኙት እኒህ ኤርትራዊያን የጀበርቲ ወንድሞቻችንና ስጋዎቻችን ማሳያ ናቸዉ፡፡ ይህ ይሆናል ብሎ ያሰበስ ማን ነበር በማለት አብራርተዋል፡፡ ሆኖም ይህ ጥናት ከመነሻ ነጥቡ ሀሳብ ጋር ማች ካላደረገ አርጎብነታችንን አርጎብነት ነዉ ማለት ነዉ እና አርጎብነቱን እንድቀጥለዉ ያደርገናል ስለዚህ ጥናቱ ተጠናቆ ሲያልቅ ዉጤቱ ምንም ሆነ ምን አዎንታዊነትም ይኑረዉ አሉታዊነት በራሱ ዉጤት ነዉ ሲሉ በሰላ ምሁራዊ አንደበት አብራርተዋል፡፡

ይህን ጥናት ለምን ዛሬ ላይማሄድ አስፈለገ፣ አሁን ሪፎርም የምናደርግበት ጊዜ አልነበር ወይ እና ለምን እስከዛሬ ያልተደረገ ነገር ዛሬ ማድረግ አስፈለ ፣ከጥናቱ ይልቅ ሪፎሙ አልነበር ወይ መቅደም የነበረበት የሚሉ ጥያቄዎች ለተነሱት የተሰጡ ምላሾች ዙርያ የድርጅ ከፍተኛ አመራሮች ጥናቱ ከ3 ዓመት በፊት የተጀመረ መሆኑን ገልጸዉ ቀድሞም ሲራ የቖየና ዛሬ የታሰበበት ያለመሆኑን አስረድተዋል፡፡ ዛሬ ላይ የአብይ ዘመን ነዉ፣ የነጻነት ዘመን ነዉ አርጎባነታችንን ጀበርቲነታችንን እንደፈለግን ሳንሸማቀቅ መናገር የቻልንበት ወቅት ላይ እንደመገኘታችን በዶ/ር አብይ ዘመን በስሙ ስያሜም ሆኖ ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በነጻነት የፈለግነዉ የምንችልበት ዘመን መሁኑም አንዱ ነዉ፡፡ አርጎባነት መጤ፣ ኢትዮጵያዊ ያልሆነ እና በኢትዮጵያዊነቱ እንዲሸማቀቅ ያደጉን ባስ ሲል ከዚያም የባሰ ሌሎች የእኛን ስነልቦና የሚሸረሽሩ ቃላቶች ሲሰነዘሩብን ስንሰደብበት የኖርን ስማችን መሆናችን ማወቅ እና መረዳት ተገቢ ነዉ፡፡ ለዚህም ወደምስራቁ ክፍል አርጎባዉን ቡዳ እያሉ መኖራቸዉ እና ኩሩዉን ማንነቱን ወደራሰቸዉ ማንነት ሲለዉጡት መኖሩን ተጠቅሷል፡፡ ይህ ከድርጅታዊ አሰራር ጋር እና ከሪፎርሙ ጋር ምንም የሚያገናኘዉ ነገር የለም ሁሉም በየፈርጁ የሚጓዝ ጉዳይ ነዉ በሚል መልስ የተሰጠ ሲሆን የመድረኩ ተሳታፊዎችም በምላሹ ሞቅ ያለ ድግግሞሽ ያለዉ ጭብጨባ ችረዋል፡፡ 

ከሌሎች የጀበርቲ ማሕበረሰብ ጋር ምን አይነት የቋንቋ መመሳሰልና ሌሎች ነገራቶች ኖረዉን ነዉ ትስስሮሹ የሚደረገዉ፡፡ በኤርትራ፣ በኢተዮጵያና በጅቡቲ የሚኖሩ አፋሮች በቋንቋና በባህል ስለሚመሳሰሉ ለመተሳሰር አልተቸገሩኝ እያጋር ያለዉ ትስስር ምንድን ነዉ፡፡ በአምስት ሀገራት የምንኖር ጀበርቲዎች እንደመሆናን ነገሩን ዉዥንብር እንዲፈጠርብ አያደርገዉም ወይ ጀበርቲ ከአርጎባ ማሕበረሰብ መጠርያ ስምነት ባለፈም የወል ስም ሆኖ ተጠቅሶ ተስተዉሏልና ነገሩን እንዴት መረመራቹሁት በርካታ ተያያዥ እኛ ተዛማጅ ጥያቄና አስተያቶች መልስ የሰጡት አዘጋጆቹ ብቻ ሳይሁኑ የመድረኩም ተሳታፊዎች ጭምር ነበሩ፡፡ ከነሱም ዉስጥ ኤርትራዊዉ ጀበርቲ ሙሰጠፋ ዓብዱልዓዚዝ በሰጡት ምላሽ ሁሉም ጀበርቲዎች ባህላዊ አለባበሳቸዉ ነቢዩ ሙሐመድ ይጠቀሙት የነበረዉ አይነት አለባበስ ነዉ፡፡ የኤርትራ ጀበርቲ ሴቶች የሚጠቀሙት የሴች አለባበስ ከኢትዮጵያዊያኑ የሚመሳሰል ነዉ፡፡ በታሪክ በቅርስ በዘር ሀረግ ተያያዝ ነን ካሉ በኋላ ዓረቦች 22 ያህል እራሳቸዉን ያቻሉ የዐረብ ሀገራት ቢኖራቸዉም ሁሉም ሲጠሩ ዓረብ ተብለዉ ነዉ፡፡ እኛም እንዲሁ መሆን እንችላለን፡፡ ጀበርት የሕብረ ብሔር ማዕቀፋችን ነዉ እና በዚህ ማዕቀፍ ዉስጥ ህብረት መስርተን የተለያዩ ፖለቲካል ኢኮኖሚካል እና ሶሻል ትብብራችንን ማጽናት እንችላለን በማለት የተናገሩ ሲሆን ከአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ከቀወት ወረዳ የመጡ ሸምገል ያሉ ተሳታፊ ደግሞ ቋንቋ አይለያየንምም፡፡ ቋንቋ አንዱ የመግባቢያ ድልድይ እንጂ ሌላ አይደለም፡፡ ዋናዉ ነገር እኛነታችንን እና እሴቶቻችንን ዳግም ማጠናከር እና ማጎልበቱ ላይ ነዉ መሰራት ያለበት ሲሉ ሁላችንንም የሚያሳምን ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የወርጂ ብሔር ተወላጅ የሆኑት ፈይሰል ወርጂ ማሕበረሰብ ምልሰተ ነገዱ እዚሁ ይፋት ተካታች መሆኑን አምነዉ ስልጤዉ፣ ሀረሪዉ፣ ወለኔዉ፣ ወርጂዉ፣ .. በሙሉ በጀበርቲ ማዕቀፍ ዉስጥ ከመሆኑ አንጻር ሁላችንንም ማንነታችንን እንደጠበቅን በጀበርቲ ሕብረ ብሔር ዉሥጥ ጠንካራ ትስስር ለመፈጠር እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡ ከአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተገኙት ሌላ ስማቸዉን ሳልይዛዉ የቀረሁት ዶ/ርም እንዲሁ ተመሳሳይ ነገሮችን በማስቀመጥ ይህ እንደመነሻ የተያዘዉ ጥናታዊ ጽሁፍ የተለያዩ፣ ሙሑራኖች አዋቂዎች የዉጪና የሀገር ዉስጥ ባለሙያዎችን አቅፎ መጠንከር እና መጎልበት እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡ 

በመጨረሻም ሰዉን ያላመሰገነ አላህንም በማለት መላዉ ተሳታፊ ለጥናት አቅራቢዎቹ፣ ለመድረክ አዘጋጆቹ እና ይህ ክስተት እንዲፈጠር ለሰሩ በሙሉ ተመስግነዉ በሸሕ አሕመደል ኩረማ የመዝጊያ ዱዓ ፕሮራሙ ተጠናቋል፡፡ 

#በእለቱ_ካስደሰቱኝ_ነገራቶች፣ ኤርትራዊያኖቹን በማግኘቴና የኤሜል እና የስልክ ልዉዉጥ በማድረጌ፣ በፌስቡክ የማዉቃቸዉ ወንድሞችን በማግኘቴ እና በጣም የማከብረዉና የምወደዉን የታሪክ አባት ሙሐመድ አቡበክርን በአካል ማየቴ እና ሸህአሕመደል ኩረማ እቅፍ አድርጌያቸዉ በመሳሜ የሆነ ደስስ የሚል ስሜት ተሰምቶኛል፡፡ 
:
ሕዳር 23፣ ዕለተ እሁድ በአዳማ ከተማ በ Ahmed Adem ተጻፈ..

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google photo

You are commenting using your Google account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.